About this episode
መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እና ያለምንም ማመንታት እንደሚነግረን መላእክት ከእግዚአብሄር በታች የሆኑ ፍጥረታትና በእርሱ እቅድና ፈቃድ ብቻ የሚመላለሱና የሚመሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በመላእክትና በእግዚእበሄር መሃል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡ ምክኒያቱም እነርሱ የእርሱ ናቸውና (መዝ. 104-4)፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግላቸውና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሄር በራሱ፤ ለእርሱም ክብር ለሚሆን አገልግሎት የተመረጡ ናቸውና (1 ጢሞ. 5፡21)፡፡ እንዲሁም እንደ እግዚአብሄር ያለ ማን ነው; የሚል ትርጉም ያለው የሚካኤል እና እግዚአብሄር ኃያል ነው የሚል ትርጉም ያለው የገብርኤል የስሞቻቸው ትርጉም በመላእክቱና በእግዚአብሄር መሃል ያለውን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቆረጠውን ግንኙነት ያሳያል፡፡