About this episode
የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የማይነጣጠሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች፣ እንዲሁም የወንጌል መሠረትና ማእከል ቢሆኑም፣ ትንሣኤው ግን ቁልፍ ክሥተት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ክርስቶስ በሕይወቱና በሞቱ የሠራቸው ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መልኩ የሚታዪቱና በአማኞች ሕይወት ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉት በክርስቶስ የትንሣኤ አካል አማካኝነት ስለሆነ ነው። በመሆኑም፣ ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረትና ማእከል ሲሆን፣ የክርስትና እምነት የመሠረት ድንጋይም ጭምር ነው።