About this episode
የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የነበረው ሕይወቱና አገልግሎቱ ማብቂያ ያገኘበት ክሥተት ስለመሆኑ ከወንጌላት ዘገባ መረዳት እንችላለን። በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ የዚህ እውነት ታሪካዊ ዳራውና ቀጥተኛ ዐውዱ የሰው ልጆች ሁሉ ሞት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት የሰውን ልጆች ክፋትና ዐመፀ ጥግ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ሲታይ ደግሞ የክርስቶስ መስቀል የሚያሳየው በሰዎች ኀጢአትና ዐመፅ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍትሓዊ ፍርድ ነው።