About this episode
መልኣክ የሚለው ቃል መጽሃፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው በሁለቱ ቋንቋዎች የሚለውን ለመረዳት መሞከር ይጠቅመናል፡፡ በእብራይስጥ ቋንቋ (mal’ak) ማልኣክ የሚል ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ (angelos) አንጅሎስ ይላል፡፡ ይህም የሚያመለክተን የመላእክት ዋናው አገልግሎታቸው እና ተግባራቸው ዜና ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች፤ አዋጅ ነጋሪዎችና መልእክተኞች እንደሆነ ነው፡፡